ኢትዮጵያ ከዴንማርክ ጋር ያላትን የፓርላማ ዲፕሎማሲ አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ኬራ ሰሚዝ ሲንድበጀርግ ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በቅርቡ የዴንማርክ ፓርላማ የውጭ ግንኙነት ኮማቴ አባላት በኢትዮጵያ የሚያደረጉትን ጉብኝትና በጉብኝታቸው ወቅት ከቋሚ ኮሚቴው ጋር የሚኖራቸውን ቆይታ አስመልክቶ ከወዲሁ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ያለመ ነው ተብሏል፡፡
በዚሁ ወቅት ዲማ ኖጎ (ዶ/ር)÷የፓርላማ ዲፕሎማሲው ኢትዮጵያ ከዴንማርክ ጋር ያላትን ግንኙነትና ትብብር እንደሚያጠናክር መግለጻቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
አምባሳደር ኬራ ስሚዝ ሲንድበጀርግ በበኩላቸው÷ ዴንማርክ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት የሚያጠናክሩ ሥራዎችን እንደምትሰራ ተናግረዋል፡፡