የብራዚል ፕሬዚዳንት የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ከቀዳማዊት እመቤት ጃንጃ ሉላ ዳ ሲልቫ ጋር በመሆን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም በዓድዋ ድል ሃውልት ስር የአበባ ጉንጉን ማኖራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።