Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ፕሬዚዳንቶች አዲስ አበባ እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ፣የኬፕ ቨርዴ ፕሬዚዳንት ጆሴ ማሪያ ፔሬራ ኔቬስና የጊኒ ቢሳዖ ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮ በ37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በጉባዔው ለመሳተፍ ዛሬ ማለዳውን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በተመሳሳይ የኬፕ ቨርዴ ፕሬዚደንት ጆሴ ማሪያ ፔሬራ ኔቬስ በጉባዔው ለመሳተፍ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የቱሪዝም ሚኒስትሯ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

እንዲሁም የጊኒ ቢሳዖ ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮም ዛሬ ማለዳ በጉባኤው ለመሳተፍ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን÷ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

እንዲሁም የሞሪታኒያ ፕሬዚዳንት ሙሃመድ ኦልድ ጋውዛኒ በ37ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሞሪሺየስ ጠቅላይ ሚኒስትር ፕራቪንድ ኩማርም የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን÷ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በመራኦል ከድር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.