የተለያዩ ሀገራት መሪዎች አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ37ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት፣ የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት እና የአንጎላ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገብተዋል።
የሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሶ ንጉዌሶ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በተመሳይ የሌሴቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳሙኤል ንፆኮአኔ ማትኬን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በተጨማሪም የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ኢመርሰን ምናንጋግዋ በ37ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
እንዲሁም የአንጎላ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጆ ሎሬንዞ በ37ኛው የኀብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።