Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) እና የብራዚል ፕሬዚዳንት በአንድነት ፓርክ የቡና ችግኞችን ተከሉ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉዊስ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ በአንድነት ፓርክ የቡና ችግኞችን ተከሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጽሕፈት ቤታቸው በተካሄደ ይፋዊ የአቀባበል ስነስርዓት በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙትን የብራዚል ፕሬዚዳንት ተቀብለዋል።

ከስድስት አስርት አመታት በላይ የቆየው የኢትዮጵያ እና የብራዚል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዋና ማጠንጠኛው ንግድ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።

ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ የሁለቱን ሀገራት ትብብር ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ እና የፀና ወዳጅነትን የበለጠ ለማጠናከር የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ ውይይት አድርገዋል።

ለፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ክብር የምሳ ግብዣም ተካሂዷል።

 

ከዚህም በኋላ ሁለቱ መሪዎች ለአካባቢ ጥበቃ ያላቸውን ቁርጠኝነት በሚያንፀባርቅ ብሎም ለቡና ባሕል ያላቸውን የጋራ አድናቆት በሚያሳይ ሁኔታ በአንድነት ፓርክ የቡና ችግኞችን ተክለዋል።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.