Fana: At a Speed of Life!

የጅቡቲና የኬንያ ፕሬዚዳንቶች በአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

 

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅቡቲ ፕሬዚዳንት እስማኤል ኡመር ጊሌ እና የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በ37ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

 

እንዲሁም የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በተመሳሳይ የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንት ቲዮዶሮ ኦቢያንግ ኒጉዬማ በኀብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.