በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስና ንግድ ባንክ አሸንፈዋል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ15ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ ከሲዳማ ቡና ጋር የተገናኙት ፈረሰኞቹ በአማኑኤል ተርፉ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን 28 አድርሷል።
ምሽት 12 ሰዓት በተከናወነ ሌላ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲል ከነማን 4 ለ 2 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ከመቻል በጊዜያዊነት ተረክቧል፡፡