አቶ አህመድ ሽዴ ከኢስላሚክ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ከኢስላሚክ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ አል ጃሰር (ዶ/ር) ጋር በኢኮኖሚ ልማት ዙሪያ ተወያይተዋል
በውይይቱ አቶ አህመድ ኢትየጵያ የተለያዩ ፈተናዎችን ተቋቁማ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጦችን እያስመዘገበች መሆኗን ገልፀዋል፡፡
ኢትየጵያ በአፍሪካ ቀንድ ኢኒሺየቲቭ ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች መሆኗን ያነሱት ሚኒስትሩ÷ የኢስላሚክ ልማት ባንክም የኢኒሺየቲቩ አባል እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኢስላሚክ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው÷ ባንኩ በኢትዮጰያ 44 ፕሮጀክቶችን በገንዘብ እየደገፈ እንደሚገኝ አንስተው÷ ለኢትየጵያ የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
በውይይቱም መጨረሻ ለሰብአዊ አገልግሎት የሚውል የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ፊርማ መከናወኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡