Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 271 የሕክምና ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሕክምና ትምህርት ቤት 271 የህክምና ተማሪዎችን አስመረቀ።

ከተመራቂዎች መካከል 158 ወንዶች ሲሆኑ÷113 ደግሞ ሴቶች ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ በሕክምና ትምህርት ዶክትሬት ዲግሪ 240፣ በጥርስ ሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ 9 እና በ ‘ቢኤስሲ’ አኔስቴዥያን ባችለር ዲግሪ 22 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ከተመራቂዎች መካከል 198 የሚሆኑት በማዕረግ፣ በከፍተኛ ማዕረግ እና በእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ እንደተመረቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመላክታል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሕክምና ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ለ52ኛ ጊዜ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.