Fana: At a Speed of Life!

9ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 9ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ አዘጋጅነት በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል።

“የዘመኑ ከተሞች ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው የከተሞች ፎረም ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የዘንድሮ ከተሞች ፎረም ከፌዴራል ከተማና መሰረት ልማት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስትና የወላይታ ዞን አስተዳደር በጋራ በመሆን የተዘጋጀ ነው።

ከየካቲት 9 እስከ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ ፎረም 125 ከተሞች ተመዘግበው እራሳቸውን ለማስተዋወቅ ቦታ የተረከቡ ሲሆን ከ50 በላይ የንግድ ድርጅቶችና የተለያዩ ተቋማት ይሳተፋሉ።

በቤዛዊት ከበደ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.