Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄዱ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበር ትልቅ ሚና እንዳለው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄዱ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅሞች ለማስከበር ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የአገልግሎቱ ሚኒስትር ዴዔታ ሰላማዊት ካሳ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ÷የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እንደሚጀምር አንስተዋል፡፡

ለህብረቱ ጉባዔ ከስድስት ወራት በፊት ጀምሮ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱንም ነው የተናገሩት፡፡

ጉባዔውን በስኬት ለማከናወን የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅቶች ሥራዎች ተጠናቅቀው በጉባዔው የሚሳተፉ መሪዎች ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡

የህብረቱ የአባል ሀገራት በጋራ ባወጡት አጀንዳ 2063 የትምህረት፣ የሳይንስና ኢኖቬሽን መስክ ላይ የተለየ ትኩረት እንዲሰጥ በአጽንኦት ማስቀመጣቸውን ተከትሎ የመሪዎች ንግግርም በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ አመላክተዋል፡፡

እንዲሁም አፍሪካውያን የአጀንዳ 2063 ግብን ለማሳካት ምን ሲሰሩ ቆይተዋል፣ ከአጋር አካላት ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምን ይጠበቃል በሚሉ ጉዳዮች ላይም መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ጠቁመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)÷የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅሞች የሚያስከብሩ ሃሳቦችን በመልዕክታቸው እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃልም ብለዋል ሚኒስት ዴዔታዋ፡፡

በየሻምበል ምህረት

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.