የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከሩዋንዳ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

February 17, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩዋንዳ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ፥ ”ከሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ እና ከኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንት ቲዎዶር ኦቢያንግ ንጉዌማ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቶቻችንን በተመለከተ ምክክር አድርገናል” ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ከኢስላሚክ ዴቨሎፕመንት ባንክ ፕሬዚዳንት ሙሃመድ አል ጃስር ጋር የልማት ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል፡፡

#Ethiopia #Ruwanda #EquatorialGuinea #IslamicDevelopmentBank

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting/ ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!