ዓለምአቀፋዊ ዜና

በሊቢያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈው መንግስት ትሪፖሊን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታወቀ

By Meseret Awoke

June 04, 2020

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27 (ኤፍቢሲ) በሊቢያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈው መንግስት ትሪፖሊን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታወቀ፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው በትሪፖሊ የሚገኘው መንግስት ለጀነራል ካሊፊ ሀፍታር ታማኝ ከሆኑ ኃይሎች የከተማዋን የአውሮፕላን ማረፊያ መንጠቃቸው ተነግሩዋል፡፡

ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያው አገልግሎት እየሰጠ እንዳልነበረ ዘገባው አስታውሶ ተግባሩን ተንታኞች ለመንግሥት ትልቅ ድል ነው ብለውታል ፡፡

በዚህ ሂደትም የቱርክ ጦር ለትሪፖሊው መንግስት ድጋፍ ማድረጉ ተነግሩዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት አዲስ ዙር የዲፕሎማሲ ግንኙነት በመጀመሩ ከሁለቱ ወገኖች የተውጣጡ አመራሮች ለድርድር ወደ ውጭ ተጉዘዋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ