የሀገር ውስጥ ዜና

118 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ

By Tibebu Kebede

June 04, 2020

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 118 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ።

ኢትዮጵያውያኑ ቦሌ አለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ጽዮን ተክሉ እና የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከዚህ ቀደም በሁለት ዙር 656 በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ መመለሳቸው ይታወሳል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

 

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።