ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በታንዛንያው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ኔሬሬ መታሰቢያ ሐውልት ምረቃ ላይ ታድመዋል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ጋር በመሆን በታንዛንያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ኔሬሬ መታሰቢያ ሐውልት ምረቃ ላይ ዛሬ ታድመዋል::
የነጻነት ታጋዩና የታንዛንያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ኔሬሬ በአፍሪካ ሕብረት ቅጥር ግቢ የመታሰቢያ ሐውልት ቆመላቸው።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት፣ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር መሐመድ ኦውልድ ጋዙዋኒ፣ የታንዛንያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን እንዲሁም የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የቀጣናዊ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
“የታንዛንያ አባት” እየተባሉ የሚጠሩት ጁሊየስ ኔሬሬ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት እንዲላቀቁ በነበረው ትግል ውስጥ ስማቸው በቀዳሚነት ከሚነሱ ሰዎች መካከል ይጠቀሳሉ።