ጠ/ ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከታንዛኒያ እና ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉህ ሀሰን እና ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ÷በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ጠ/ ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡
የጋራ ግባቸው በሆነችው የለማች እና የተረጋጋች አፍሪካን እውን ማድረግ ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጋቸውንም ገልፀዋል፡፡