ኢትዮጵያ እና ሞሪሺየስ ግንኙነታቸውን ለማሳደግ ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሞሪሺየስ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የካቢኔ ፀሐፊ እና የሲቪል ሰርቪስ ኃላፊ ፕሬሞዴ ኔሩንጁን ጋር ተወያይተዋል።
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ጉዳይ ቁርጠኛ መሆኗን እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ከሞሪሺየስ ጎን እንደምትቆም አምባሳደር ምስጋኑ ተናግረዋል።
ሁለቱ ወገኖች በንግድ፣ በቱሪዝም፣ በአቪዬሽን እና በግብርና ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የሁለትዮሽ ግንኙነቱን በማጠናከር የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባም የተገለፀ ሲሆን÷በቀጣይ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማሳለጥ አሰራሮችን በተለያዩ ደረጃዎች መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።