Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 5 ዓመት 9ኛ የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በጉባዔው በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የሚቀርበውን የአስፈፃሚ አካላት የ6 ወራት አፈጻጸም እንደሚያዳምጥ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ ም/ቤት፣ የጠቅላይ ፍ/ቤትና የዋናው ኦዲት የግማሽ በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው ሃሳብና አስተያየት ተሰጥቶባቸው እንደሚጸድቁም ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.