Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ምክር ቤት 7ኛ መደበኛ ጉባኤ ከነገ በስቲያ መካሄድ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከየካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ገለጹ።

የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ ምክር ቤቱ ከየካቲት 13 እስከ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በሚያካሄደው መደበኛ ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር አስታውቀዋል።

በጉባኤው የክልሉ የአስፈፃሚ አካላት የ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እንደሚቀርብ ተናግረዋል።

በቀረበው ሪፖርት ላይ የምክር ቤት አባላት ከተወያዩ በኋላ ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በክልሉ ተከስቶ የነበረውን የሰላም እጦት ችግር ለመፍታት ከህዝብ ጋር ሰፊ ውይይት መደረጉን ያስታወሱት አፈ ጉባኤዋ፣ በዚህም የክልሉ ሰላም እየተሻሻለ መምጣቱን ነው የገለጹት።

ሰላሙን በተሟላ መንገድ በመመለስ የክልሉን ልማት አጠናክሮ ለማስቀጠል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ምክር ቤቱ ከተወያየ በኋላ ቀጣይ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥም ጠቅሰዋል፡፡

በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተለያዩ ሹመቶችን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.