Fana: At a Speed of Life!

87ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ተከበረ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 87ኛው የየካቲት 12 መታሰቢያ በአዲስ አበባ ሥድስት ኪሎ የሰማዕታት ሐውልት ተከብሯል፡፡

ዕለቱ የአዲስ አበበ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የታሰበው፡፡

6 ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታት ሐውልትም ከንቲባ አዳነች የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ከንቲባዋ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ የዛሬዋን መልክ የያዘችው በአባቶቻችንና በእናቶቻችን ውድ መስዋዕትነት ነው ብለዋል።

ለነፃነታችንና ለሰላማችን የተከፈለልንን መስዋዕት በመገንዘብ ሰላምን በማፅናት ሀገራችንን ልንጠብቅ ይገባል ሲሉም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

የጥንታዊት ጀግኖች ዓርበኞች ማህበርፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ በበኩላቸው÷ በጀግኖች ዓርበኞች የተከፈለው መስዋዕትነት ዋጋ የሚኖረው እንዲህ በክብር ሲታሰብ ነው ብለዋል፡፡

መንግሥት ለኢትዮጵያ ነፃነትና ክብር ለተዋደቁ ዓርበኞች እየሰጠ ስላለው ክብርም ምስጋና አቅርበዋል ።

የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም በአዲስ አበባ በፋሺስት ጣሊያን በግፍ የተጨፈጨፉ ሰማዕታትን በማሰብ፤ ሥድስት ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታት ሐውልት የአበባ ጉንጉን በማኖር በየዓመቱ ይታሰባል፡፡

በምንተስኖት ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.