ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር ) ከዩኒዶ ዋና ዳይሬክተር ጋር መከሩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ዋና ዳይሬክተር ገርድ ሙለር ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸውም በኢኮኖሚ ሪፎርሙና በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ዙሪያ ሚኒስትሯ ገለጻ አድርገዋል፡፡
ገርድ ሙለር በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ከፍተኛ አቅም ያላት ሀገር ናት ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህ አቅም ልክም ኢንቨስትመንት ለመሳብ ጥረት ማድረግና መጠቀም እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡