አቶ አሕመድ ሺዴ ከአሜሪካ ልዑካን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ሞሊ ፊ፣ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋን ጋር ተወያይተዋል።
ሚኒስትሩ ለአሜሪካ የልዑካን ቡድን ስለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሁኔታ፣ ተስፋዎች እና እየተካሄዱ ያሉ የማክሮኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ ለዕድገትና ለስራዎች ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሁለቱ ወገኖች ኢትዮጵያ ከግጭት በኋላ ያላትን ኢኮኖሚ፣ ማገገም እና ሰብዓዊ ድጋፎችን አስመልክቶ በጋራ ለመስራት፣ ከአይኤምኤፍ እና ዓለም ባንክ ድጋፍ ማሰባሰብ ላይ ገንቢ የሚባል ውይይት መደረጉም ነው የተገለጸው፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!