ቢዝነስ

የሕንድ ንግድና ኢንቨስትመንት ልዑክ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎቱን ገለጸ

By Mikias Ayele

February 20, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕንድ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ልዑክ በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመን ዘርፎች ላይ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡

ልዑኩ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሮች ዳጋቶ ኩምቤ እና ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) ጋር በአዲስ አበባ ተወያይቷል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ በፋርማሲቲካል፣ በጨርቃጨርቅ፣ በአይ ሲ ቲ፣ በግብርና እና ሌሎችም ዘርፎች ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ልዑኩ ማሳወቁን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የሕንድ ንግድና ኢንቨስትመንት ልዑክ በኢትዮጵያ ለሚያከናውኑት ኢንቨስትመንት መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያድርግ ምክትል ኮሚሽነሮቹ አረጋግጠዋል፡፡