የሀገር ውስጥ ዜና

የድርሻ ገበያ እና ልውውጥ መጀመር ኢትዮጵያ የእድገት ትልሟ እውን እንዲሆን አዳዲስ ካፒታል በመሳብ ጨዋታ ቀያሪ ይሆናል- ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

By Feven Bishaw

February 20, 2024

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የድርሻ ገበያ እና ልውውጥ (ስቶክ ማርኬት ኤንድ ኤክስቼንጅ) መጀመር ኢትዮጵያ የእድገት ትልሟ እውን እንዲሆን አዳዲስ ካፒታል በመሳብ ጨዋታ ቀያሪ ይሆናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ቦርድ÷ ኢትዮ ቴሌኮም ሕዝባዊ ለመሆን ያለውን ዝግጁነት እና የካፒታል ማርኬት ባለስልጣን በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያን ወደሥራ በማስገባት ላይ የደረሰበትን ደረጃ ገምግሟል፡፡

ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ በኢትዮጵያ የድርሻ ገበያ እና ልውውጥ (ስቶክ ማርኬት ኤንድ ኤክስቼንጅ) መጀመር ኢትዮጵያ የእድገት ትልሟ እውን እንዲሆን አዳዲስ ካፒታል በመሳብ ጨዋታ ቀያሪ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ይህም ለሀገራችን አጓጊ አዲስ ምዕራፍ ነው ብለዋል፡፡