Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን በጋምቤላ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

ጉባኤው በሚኖረው የሁለት ቀናት ቆይታ የክልሉን የ2016 የግማሽ ዓመት የልማትና መልካም አስተዳደር እቅድ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የስራ ክንውን ሪፖርት አድምጦ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

እንዲሁም የቀጣይ ግማሽ ዓመት የተከለሰ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅድ፣ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችና ሌሎች ውሳኔዎችን አዳምጦ ውሳኔ እንደሚያሳልፍም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በጉባኤው ላይ የምክር ቤቱ አባላትን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የሥራ ሀላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የሐይማኖት አባቶች እየተሳተፉ ነው።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.