Fana: At a Speed of Life!

የአፋር፣ አማራና ትግራይ ክልሎችን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር፣ የአማራና ትግራይ ክልሎች መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማጠናከር ያለመ ኮንፈረንስ በሰመራ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በኮንፍረንሱ ከሶስቱም ክልሎች የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት፣ ከነጋዴዎች ማህበራትና ከግል ዘርፍ የተውጣጡ አካላት እየተሳተፉ ነው።

ኮንፍረንሱ ባለፉት ጊዜያት በክልሎቹ አጎራባች አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ችግር ምክንያት የተቀዛቀዘውን የንግድ እንቅስቃሴ መልሶ ለማነቃቃት ሲሆን÷ የግል የንግድ ሴክተሩም መንቀሳቀስ እንዲችል ያለመ ነው ተብሏል።

መርሐ ግብሩን የሰላም ሚኒስቴር፣ የአፋር ንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤትና በዘርፉ የሚንቀሳቀስ ግብረ ሰናይ ድርጅት በትብብር ያሰናዱት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በኮንፍረንሱ ሰላም ሚኒስቴርና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ተወካዮች እንዲሁም የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮና፣ የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊዎች ታድመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.