አሸናፊ ከተሞች የሚለዩበት የዳኞች የምዘና መስፈርት ላይ ዉይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከየካቲት 9 ጀምሮ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘዉ 9ኛዉ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም አሸናፊ ከተሞች የሚለዩበት የዳኞች የምዘና መስፈርት ላይ ዉይይት እየተካሄደ ነው።
ፎረሙ ዛሬም በተለያዩ መርሃ ግብሮች የቀጠለ ሲሆን÷ የከተሞች ዉድድርን እንዲዳኙ የተመረጡ ኮሚቴዎች ለተሳታፊ ከተሞች ተወካዮች የዉድድር መስፈርቱን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ዳኝነትቱን በሚስጢር ሲያካሂዱ የነበሩ ዳኞች እንደገለፁት፤ ከተሞች በፎረሙ ላይ ያቀረቡት ይዘት እና ገለፃቸዉ ይመዘናሉ።
በመድረኩ በከተማ ግብርና፣ በሌማት ትሩፋት እና በማዕድ ማጋራት፣ ሀገር አቀፍ የልማት ፕሮጀክቶችን ድህነትን ለመዋጋት ምን ያህል ተጠቅመዉበታል የሚሉት መመዘኛ መስፈርቶች እንደሆኑ ተጠቁሟል።
ከተሞች ኢንቨስተሮች እና ቱሪስቶችን ለመሳብ፣ ገቢያቸዉን ለማሳደግ እና ለመጠቀም ያደረጉት ጥረትም ሌላኛዉ መመዘኛ መስፈርት መሆኑም ተጠቁሟል።
1ኛ ፣ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ የወጡ ከተሞች ከሚያገኙት ዕዉቅና ባሻገር የዋንጫና የተለያየ መጠን ያለው ስክሪን የሚሸለሙ ይሆናል ተብሏል።
ዉድድር ዉስጥ የማይገቡት አዲስ አበባ፣ ሸገር ከተማ እና አዘጋጇ ወላይታ ሶዶ ከተማ የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ሽልማት ይበረከትላቸዋል።
ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሚኖረዉ የማጠቃለያ መርሐ ግብር አሸናፊ ከተሞች ይፋ የሚደረጉ ይሆናል።
በምንተስኖት ሙሉጌታ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!