ኤጀንሲው ከ700 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን ሕንፃ ከነገ በስቲያ ያስመርቃል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ -መዛግብትና ቤተ -መፃሕፍት ኤጀንሲ ከ700 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን ሕንፃ ከነገ በስቲያ በይፋ እንደሚያስመርቅ አስታወቀ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ይኩኖ አምላክ መዝገቡ÷ የሕንፃውን ምርቃት አስመልከተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው ኤጀንሲው አዲስ ያስገነባውን ሕንፃ ሲያስመርቅ የተቋቋመበትን 80ኛ ዓመትም አብሮ የሚያከብርበት ዕለት መሆኑን ተናግረዋል።
አዲሱ ሕንፃ 17 ወለሎች ያሉትና ከ700 ሚሊየን ብር በላይ በመንግስት ወጪ ተደርጎበት የተገነባ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
ሕንፃው የመዛግብት ማከማቻ እንደመሆኑ ዘመኑን ባገናዘበ መልኩ በቴክኖሎጂ ተደግፎ የተገነባ መሆኑን አንስተዋል።
ህንፃው ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ አንባቢያን፣ መፅሐፍ አዟሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የፊታችን ቅዳሜ ይመረቃል ተብሏል፡፡
በቅድስት ብርሃኑ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!