Fana: At a Speed of Life!

9ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከየካቲት 9 ጀምሮ በወላይታ ሶዶ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 9ኛዉ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የመዝጊያ ሥነ-ስርዓት ተካሄደ።

በመዝጊያ ሥነ-ስርዓቱ ላይም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ፎረሙ ከተሞች መሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ የሴፍቲኔት፣ ምግብ ዋስትና እና ሌሎች መሰል ዘርፎች ያካተተ ልምድ የተለዋወጡበት መድረክ እንደነበር ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

ከተሞች ይህንን የልምድ ልውውጥ በማጠናከር ወደ ተሻለ ብልፅግና መሻገር እንደሚገባ በማንሳት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያለውን ቅሬታ መፍታት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ለሰባት ተከታታይ ቀናት በወላይታ ሶዶ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 9ኛው የከተሞች ፎረም ስኬታማ እንደነበርም ነው ሚኒስትሯ የጠቀሱት፡፡

124 ከተሞች ተሳታፊ በሆኑበት በዚህ ፎረም ከተሞች በ4 ምድቦች ተከፍለው ለየምድቡ በቀረቡ የመወዳደሪያ መስፈርቶች ተመዝነዋል።

በዚህም ከምድብ 1- አዳማ፣ ሀዋሳ እና ደሴ÷ ከምድብ 2- ቡታጅራ፣ ባሌሮቤ እና ነቀምቴ÷ ከምድብ 3- ከሚሴ፣ ወራቤ እና ሊሙገነት÷ ከምድብ 4- ኮንሶ ካራት፣ ግልገል በለስ እና እምድብር ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት የውድድሩ አሸናፊዎች ሆነዋል።

አስተናጋጇ ወላይታ ሶዶ፣ አዲስ አበባ እና ሸገር ከተሞች ደግሞ የ9ኛው የከተሞች ፎረም ልዩ ተሸላሚዎች ሆነዋል።

ሰመራ ከተማ 10ኛውን የከተሞች ፎረም ለማዘጋጀት መመረጧም ተገልጿል፡፡

በቤዛዊት ከበደ እና ምንተስኖት ሙሉጌታ

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.