ስፓርት

 ኢትዮጵያ ሁለት የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ውድድሮችን እንድታስተናግድ ተመረጠች

By Mikias Ayele

February 23, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ሁለት የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ውድድሮችን እንድታስተናግድ በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ማህበር ተመርጣለች፡፡

የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ ማህበራት ምክር ቤት ዛሬ በኬኒያ ባደረገው ጉባኤ ነው ኢትዮጵያ ውድድሮችን እንድታስተናግድ መመረጧን ያስታወቀው፡፡

በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ የሴካፋ የሴቶች እግር ኳስ ሻምፒየንስ ሊግ እና ከ20ዓመት በታች ሴቶች ውድድሮችን ታስተናግዳለች።

ዩጋንዳ ከ 17 ዓመት በታች ወንዶች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያን ታንዛኒያ የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ማጣሪያ እና ዛንዚባር የሴካፋ ዋናውን ውድድር እና የአፍሪካ ትምህርት ቤቶች ማጣሪያ እንዲያስተናግዱ የተመረጡ አገራት ናቸው።

በወርቅነህ ጋሻሁን