በተመረጡ የግል ጤና ተቋማት የኮቪድ-19 እና መደበኛ ክትባቶችን መስጠት ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተመረጡ የግል የጤና ተቋማት የኮቪድ-19 ክትባትን ከሌሎች መደበኛ ክትባቶች ጋር መስጠት የሚያስችል አዲስ አሰራር መጀመሩን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ÷ክትባቱ ከመንግስት የሕክምና ተቋማት በተጨማሪ በተመረጡ የግል የጤና ተቋማት እንዲሰጥ መደረጉ ከግሉ የጤና ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር ያጠናክራል ብለዋል፡፡
በከተሞች 35 በመቶ የሚሆነው ህብረተሰብ የጤና አገልግሎቱን የሚያገኘው ከግል የጤና ተቋማት መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
ይህም በ2030 የእናቶችና ህጻናት ሞት ለመቀነስ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የግል የጤና ተቋማት አስተዋጽኦ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ጥራት ያለው የክትባት አገልግሎት፣የተጠናከረ የቀዝቃዛ ሰንሰለት ስርዓት፣ ወቅቱን የጠበቀ የክትባት አቅርቦት እና ዘመኑን የዋጀ የሪፖርት አቀራረብ ዘዴ በትኩረት ክትትል እንደሚደረግባቸው ጠቅሰዋል፡፡
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጆናታን ሮስ በበኩላቸው ÷የግሉ ጤና ሴክተር በሚፈለገው ልክ ያልተጠናከረና በጅምር ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም በከተሞች አካባቢ ግን በፍጥነት እያደገ ነው ብለዋል፡፡
አሁን አሁን በርካታ ታካሚዎች የግል ጤና ተቋማትን እየተጠቀሙ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከግል የጤና ተቋማት ጋር በትብብር መስራት መጀመሩ ዘርፉን ያሳድገዋል ነው ያሉት።
አገልግሎቱ በተመረጡ አርባ የሕክምና ተቋማት በተለይም በግጭት ምክንያት የተጎዱ በ7 የሀገሪቱ ክልሎች እና 2 የከተማ መስተዳድሮች እንደሚሰራ መገለጹን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!