ፋና ስብስብ

አንዲት እናት 4 ልጆች በሰላም ተገላገለች

By Feven Bishaw

June 05, 2020

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በስልጤ ወረዳ አንዲት እናት 4 ልጆች በሰላም መገላገሏ ተሰማ።

የወረዳው ሰነና ገሬራ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወይዘሮ ዜኖ ሸምሱ በቅበት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተደረገላት የቀዶ ህክምና 3 ሴት እና 1 ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግላለች።