Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በአዲሱ የምክር ቤቱ ቋሚ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ማከናወን ጀምሯል::

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩን የ2016 የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ለምክር ቤቱ እያቀረቡ ይገኛል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሪፖርታቸው የኑሮ ውድነትን ለማቃለል የምርት አቅርቦትን የማሻሻል፣ በቴክኖሎጂ በመታገዝ የንግድ ስርዓቱን የማዘመን፣ የቁጥጥርና የክትትል ስራን የማጠናከር ስራ በትኩረት በመሰራት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የፍጆታ ምርቶችን ወደ ከተማዋ በስፋት በማስገባት ከአምራች እስከ ተጠቃሚ ያለውን የግብይት ሰንሰለት በማሳጠርና፡ ዘመናዊ የግብይት ስርዓትን በመፍጠር ሸማቹ ህብረተሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርት ማግኘት እንዲችል መሰራቱን ጠቁመዋል፡፡

በሜጋና ሌሎች ፕሮጀክቶች በግማሽ ዓመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በተመለከተ ያነሱት ከንቲባዋ÷ የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች 24/7 የአሰራር መርህ ባህል ተደርጎ እየተተገበረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ በ2016 በጀት ዓመት በአጠቃላይ በግንባታ ሂደት ላይ ከነበሩት 14 የተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ውስጥ የአድዋ መታሰቢያ የተጠናቀቀ ሲሆን÷ ያልተጠናቀቁ ትኩረት የሚሹ ትልልቅ ፕሮጀክቶች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

በአጠቃላይ ትኩረት የሚፈልጉና በተገቢው ፍጥነት ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በቀሪ ወራቶች ከፍተኛ ርብርብ ይደረጋል ማለታቸውን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.