የሀገር ውስጥ ዜና

በአራዳ ክ/ከተማ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው

By Melaku Gedif

February 25, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሕዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

የውይይት መድረኩ “ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና”በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡

በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የኦሮሚያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲና በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተገኝተዋል፡፡