የሀገር ውስጥ ዜና

በትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By ዮሐንስ ደርበው

February 25, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

አደጋው ዛሬ ከሰዓት 10 ሠዓት አካባቢ መድረሱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጠዋል፡፡

አደጋው የደረሰውም ከአዲስ አበባ ወደ ቡታጅራ ይጓዝ የነበረ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ 7 ሰዎችን ከጫነ “ባጃጅ” ጋር በመጋጨቱ ነው ብለዋል፡፡

የአምስቱ ተጓዦች ሕይወት ወዲያውኑ ማለፉን እና በሁለቱ ላይም ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ጠቅሰዋል፡፡

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችም በወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ሆስፒታል ሕክምና እያገኙ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው