ባለፉት 5 ዓመታት የተካሄዱ የአዲስ ወግ ውይይቶችን የሰነደ “የአዲስ ወግ መድረኮች” መጽሐፍ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አምስት ዓመታት የተካሄዱ የአዲስ ወግ ውይይቶችን የሰነደ “የአዲስ ወግ መድረኮች” መጽሐፍ በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡
በመርሐ-ግብሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም÷ ከርዕሰ ጉዳይ መረጣና አሳታፊነት አንጻር የመድረኩን የአምስት ዓመት ጉዞ ቃኝተዋል፡፡
የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ አዲስ ወግ ለፖሊሲ ግብዓት ሆኖ ማገልገሉን ጠቁመዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት÷ አዲስ ወግ ቀጣይነት ያለው የውይይት ባህልን ያዳበረ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የታሪክ ምሁሩ ታምራት ሃይሌ (ዶ/ር)÷ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውይይት ታሪክ ዳስሰዋል፡፡
ጋዜጠኛ ዳዊት መስፍን አዲስ ወግ በመገናኛ ብዙኃን የተሰጠውን ሽፋን የተመለከተ ጥናታዊ ዳሰሳ ማቅርቡን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቋሚ ዘጋቢዎችም መድረኩን በመዘገብ የነበራቸውን ልምድ አካፍለዋል፡፡