Fana: At a Speed of Life!

 በአማራ ክልል በ4 ቢሊየን ብር ወጪ ሶስት አዳሪ ት/ቤቶች እንደሚገነቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በ4 ቢሊየን ብር ወጪ ሶስት አዳሪ ትምህርት ቤቶች እንደሚገነቡ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው ሃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) እና የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ  ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ በጎንደር ከተማ የአዳሪ ት/ቤት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል ።

ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷  የአዳሪ ትምህርት ቤቶች መገንባት የተሻሉ ተማሪዎች ሙሉ ጊዜያቸውን ትምህርታቸው ላይ እንዲያውሉ ያስችላል።

ለትምህርት ጥራት የጋራ ርብርብ በማድረግ ትውልድን የመገንባት ሥራ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም አሳሰበዋል።

በክልሉ ሶስት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በ4 ቢሊየን ብር ወጪ እንደሚገነቡ መናገራቸውን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ ባለሃብቶች  እና ዳያስፖራዎች ለትምህርት ዘርፉ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.