Fana: At a Speed of Life!

የተሃድሶ ስልጠና ላጠናቀቁ የቀድሞ ልዩ ኃይል አባላት የአቀባበል ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል የቀድሞ ልዩ ሀይል አባላት የነበሩት የተሠጣቸውን የተሀድሶ ስልጠና ወስደው ላጠናቀቁና በደሴ ከተማና በደቡብ ወሎ ዞን ለተመደቡ የፀጥታ አባላት አቀባበል ተደረገላቸው።

በአቀባበል ሥነ-ስርዓቱ የደቡብ ወሎና የደሴ ከተማ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ብርጋዴል ጀኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ፣ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አሊ መኮንን፣ የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ም/ከንቲባና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ፥ አመራሮችና የጸጥታ አካላት የህዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት እየሠራን ነው ብለዋል።

የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ ጦርነት ሳይሆን ሠላም፣ ውይይትና ንግግርን አማራጭ አድርገን እየሠራን ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የሚደረገውን ግጭት በማቆም ጥያቄዎችን በሠላም ለመፍታት አሁንም የሰላም ጥሪው ክፍት መሆኑን አስገንዝበዋል።

የደሴ ከተማና የደቡብ ወሎ ዞን በጋራ ሆነን ስለሠላም ለምናደርገው ስምሪት በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል ምክትል ከንቲባው።

የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን በበኩላቸው፥ የአማራ ህዝብ ህግን የሚያከብር፣ ሀገርን የሚያስጠብቅ፣ ለኢትዮጵያ የሚታገል ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ግን የተለያዩ ችግሮች አጋጥሞታል፤ ይሄንን የምንፈታው በጋራ በመመካከርና በመግባባት ነው ሲሉ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የደቡብ ወሎና የደሴ ከተማ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ብርጋዴል ጀኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ በበኩላቸው፥ የተሃድሶ ስልጠና የወሰዱ የቀድሞ ልዩ ኃይል አባላት ከመከላከያ ጋር በመሆን የሀገርን ሠላም እንደሚያስጠብቁ ጠቁመዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.