Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከጁሊየስ ጋርቬይ (ዶ/ር) ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ትግል ቀደምት አቀንቃኝ ማርከስ ጋርቬይ ልጅ ጁሊየስ ጋርቬይ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ታዬ÷ ማርከስ ጋርቬይ ለፓን-አፍሪካኒዝም ንቅናቄ እና ለጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ትግሎች መሰረትን የጣሉ አርአያ-ሰብ መሆናቸውን አውስተዋል፡፡

መሰል ፈር ቀዳጅ ቀደምት አባቶች ሊታወሱ እና ሊዘከሩ ይገባል ማለታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

ጁሊየስ ጋርቬይ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ በመላው ዓለም የሚገኙ ጥቁር ሕዝቦች ኢትዮጵያን የነፃነታቸው ባለውለታ አድርገው እንደሚቆጥሯትና ለኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

ጁሊየስ ጋርቬይ (ዶ/ር) ከቀናት በፊት የዓለም የጥቁር ታሪክ፣ ቅርስ እና ትምህርት ማዕከል የበላይ ጠባቂ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.