የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የጅቡቲ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

February 26, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ የጅቡቲ አምባሳደር አብዲ ማህሙድ ኢቤ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም÷በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡