Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የፍትሕ ተቋማት የጋራ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር አቀፍ የፍትሕ ተቋማት የጋራ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፍትሕና የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የፍትሕ ቢሮ የሥራ ኃላፊዎችና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎችም ተሳትፈዋል።

ለአራት ተከታታይ ዙሮች የተካሄዱት የፍትሕ ተቋማት የጋራ መድረኮች ወጥ የሆነ የፍትሕ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ቅንጅታዊ አሰራር እንዲጎለብት ማስቻሉም ነው የተነሳው።

ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው 5ኛው የፍትሕ ተቋማት መድረክ ደግሞ በርካታ ጉዳዮች እንደሚነሱበት ኢዜአ ዘግቧል።

የ2016 ዓ.ም የፍትሕ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ተግባራት፣ ሀገራዊና የክልሎች የተጠቃለለ የስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርትም ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.