Fana: At a Speed of Life!

20 ሚሊየን ወጣቶችን በስልጠና ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣዮቹ ስምንት ዓመታት 20 ሚሊየን ወጣቶችን ለማሰልጠን እና 10 ሺህ ወጣቶችን በአሰልጣኞች ስልጠና ተደራሽ ለማድረግ ያለመ የለውጥ ትውልድ የተሰኘ ስምምነት ተፈረመ፡፡

ስምምነቱ የተፈረመው በሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ብሬክ ስሩ ትሬዲንግ አ.ማ ድርጅት መካከል ነው፡፡

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለጹት÷ ሀገራችንን ወደ ብልጽግና ለማሻገር በሚደረገው ጥረት የወጣቶችን አስተሳሰብ በማልማት የለውጥ ትውልድ መፍጠር ዋነኛ መንገድ ነው፡፡

ተከታታይነት ያላቸው የሰብዕና ልማት፣ የአስተሳሰብ ለውጥ የልቦና ውቅርን የሚያስተካክሉ ስልጠናዎች መስጠትም ሀገራችን ለጀመረችው የለውጥ ጉዞ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ስልጠናዎችና መርሐ-ግብሮችም ሚኒስቴሩ ከብሬክ ስሩ ትሬዲንግ አ.ማ ጋር በመተባበር እንደሚሰጥ ጠቁመዋል፡፡

የብሬክ ስሩ ትሬዲንግ የቦርድ ስብሳቢ ነጻነት ዘነበ በበኩላቸው÷ የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ ለሀገራቸውና ለወገናቸው ማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶችን ማብቃት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ስልጠናውም በቀጣዮቹ ስምንት ዓመታት በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አሥተዳደሮች እንደሚተገበር ጠቁመው÷ በዚህም 20 ሚሊየን ወጣቶችና 10 ሺህ ወጣቶች በአሰልጣኞች ስልጠና ተደራሽ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.