Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋ የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋናው መስሪያ ቤት ጉብኝት አደረገ።

ከጉብኝቱ በኋላም ልዑኩ ከአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እና የአየር መንገዱ ማኔጅመንት አባላት ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጉ ተገልጿል፡፡

በዚሁ ወቅትም ስለ አየር መንገዱ አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ለልዑኩ ገለፃ መደረጉን የአየር መንገዱ መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.