አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ልጆችን ተገላገለች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤንች ሸኮ ዞን ኮሰኮል ቀበሌ ነዋሪ የሆነች አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ሕጻናትን ተገላገለች፡፡
ከአራቱ ሦስቱ ወንዶች መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡
ሕጻናቱ በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የእናቶችና ጨቅላ ሕጻናት ሕክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑም ተገልጿል፡፡
እያንዳንዳቸውም ከ1 ነጥብ 3 እስከ 1 ነጥብ 7 ኪሎ ግራም እንደሚመዝኑ ተጠቅሷል፡፡