ስፓርት

ፖል ፖግባ ለ4 ዓመታት ከእግር ኳስ ጨዋታ ታገደ

By Tamrat Bishaw

February 29, 2024

ፖግባ በጣሊያን ብሄራዊ ጸረ- አበረታች ቅመሞች ቡድን ከባለፈው መስከረም ወር ጀምሮ ምርመራ ሲደረግበት መቆየቱ ተጠቅሷል፡፡

በተደረገው ምርመራም የ30 ዓመቱ አማካይ አበረታች ንጥረ ነገር (ዶፒንግ) መጠቀሙ ተረጋግጧል ።

ፖግባ ከቱሪኑ ክለብ ጁቬንቱስ ጋር የሁለት ዓመት ቀሪ ኮንትራት የሚቀረው ሲሆን÷ ቅጣቱን ተከትሎ ድጋሚ በክለቡ መለያ የመታየቱ ጉዳይ አጠራጣሪ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡