የኤች አይ ቪ መከላከል ጉባዔ በጋምቤላ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የኤች አይ ቪ (ኤድስ) መከላከል ጉባዔ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በጋምቤላ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩም የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ የጤና ሚኒስቴር ዴዔታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ ፣ የጋምቤላ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ተንኩዌይ ጆክን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ጉባዔው በሚኖረው የአንድ ቀን ቆይታ የኤች አይ ቪ(ኤድስ) ወረርሽኝ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል በተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡