Fana: At a Speed of Life!

የውሃ ፕሮጀክቶች ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ ፕሮጀክቶች ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሃብት አስተዳደር ሥራዎችን ለመደገፍ በኢትዮጵያ ካሉ 12 ተፋሰሶች ውስጥ ለልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ባላቸው በተወሰኑ ተፋሰሶች ላይ በተቀናጀ መልኩ ለማልማት ዕቅድ ይዞ እየሰራ ይገኛል ።

እነዚህም ዓባይ ፣ አዋሽ ፣ ዋቢ ሸበሌ፣ ሪፍት ቫሊ ሃይቅ ፣ ኦሞ ጊቤ ፣ ዳናክል እና ተከዜ መሆናቸው በመድረኩ ተገልጿል ።

የውሃ ፕሮጀክቶቹ ከኔዘርላንድስና ከጣልያን መንግስት እንዲሁም ከአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ እርዳታና ብድር በተገኘ ድጋፍ እንደሚሰሩ ተጠቅሷል፡፡

ኢትዮጵያ ውሃ ሃብት አጠቃቀም በሀገራዊ ንቅናቄ መልኩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች እንደምትገኝ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ኢ/ር ዶ/ር) ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ አምባሳደር ሄንክ ጃን ሄከር በበኩላቸው÷ በውሃ ሃብት አስተዳደርና አጠቃቀም ላይ በጋራ በመስራት የሚገኘው ጥቅም የሁላችንም ነው ብለዋል ።

በመድረኩ ብሔራዊ የተቀናጀ የውሃ ሃብት አስተዳደር ፕሮግራም ዙሪያ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።

በምንተስኖት ሙሉጌታና አሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.