ለሀገር ክብር መቆምን ከዓድዋ የድል መንፈስ መማር እንደሚገባ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ውስጣዊ አንድነትን በማጠንከር ለሀገር ክብር መቆምን ከዓድዋ የድል መንፈስ መማር ይገባል ሲሉ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አስገነዘቡ፡፡
“ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ሐሳብ 128ኛው የዓድዋ ድል በአየር ኃይል ተከብሯል።
ሌተናል ጄኔራል ይልማ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ የዓድዋ ድል ኢትዮጵያዊያን አንድነታቸውንና ኅብረ ብሔራዊነታቸውን በተግባር ያረጋገጡበት ነው ብለዋል።
በውጭ ሀገር ሆነው የሠራዊቱን ስም ለማጉደፍ የሚረባረቡ የጥፋት ቡድኖችን ሴራ ማክሸፍ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
የአየር ኃይል አባላትም የሥነ-ልቦና አቅማቸውን በማሳደግ ኢ-ተገማች የሆነውን ዓለማዊ እና ቀጣናዊ ሁኔታ ያገናዘበ ዝግጁነታቸውን በተግባር ሊያረጋግጡ ይገባል ነው መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።