Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች የተከበረው 128ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በሰላም ተከብሮ ተጠናቋል – የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች የተከበረው 128ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ መርሃ-ግብር በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡

የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ/ም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ፣ የኢፌዲሪ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የታደሙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ የተከበረው 128ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በሰላም እና በልዩ ድምቀት መከበሩንም የጋራ ግብረ-ኃይሉ ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዓሉ በአዲስ አበባ አዲስ በተገነባው በአድዋ ድል መታሰቢያ በደማቅ ስነ ስርዓት በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን እቅድ በማውጣት የሚጠበቅበትን ኃላፊነትና ተግባር ማከናወኑን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ገልጿል፡፡

ለበዓሉ በሰላም መከበር ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ አካላት አመራሮችና አባላት እንዲሁም በተለያየ መልኩ የፀጥታውን ስራ ለደገፉ በጎ ፈቃደኞች እንዲሁም ለመላው የከተማችን ነዋሪዎች ግብረ ኃይሉ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.