የሀገር ውስጥ ዜና

የሕዝባችንን ፈተናዎች እና ፍላጎቶች ማዳመጥ ቀዳሚ ተግባራችን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

By Melaku Gedif

March 04, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁሉም አካባቢ የሚኖረውን ሕዝባችንን ፈተናዎች እና ፍላጎቶች ማዳመጥ ቀዳሚ ተግባራችን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሲዳማና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ከተወጣጡ ተወካዮች ጋር መወያየታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በዚህ ወቅትም በሁሉም አካባቢ የሚኖረውን ሕዝባችንን ፈተናዎች እና ፍላጎቶች ማዳመጥ ቀዳሚ ተግባራችን ነው ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡